ለመመለስም ሃገር ያስፈልጋል

Document

እንኳን ደስ አላችሁ

ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ በስደት በሠው ሀገር በእንግልትና በስቃይ ላይ የነበሩ እህት ወንድሞቻችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሂደቱ ቀጥሎ ሠሞኑን መሬቷን ተንበርክከው እየሣሙ ሀገራቸው የገቡ እህት ወንድሞችን አይተናል እንኳን በሠላም ለሀገራችሁ ለወገናችሁ በቃችሁ ፣ ከሚወዳችሁ ዘመድ ወገናችሁ ጋር በመገናኘታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ 🎉🌹🎉 አሁንም በሠው ሀገር በስደት በስቃይና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያላችሁ እህት ወንድሞች አይዟችሁ ሀገር ወገን አላችሁ ቀናችሁ ደርሶ እናንተም በቅርብ ግዜ ለሀገራችሁ እንደምትበቁ ሙሉ ተስፋ አለን 🙏🙏🙏 ሀገራችን ከስደት ቢከፋን ተመልሶ መኖሪያችን መጠለያችን ነችና ሁሉ ነገር በሀገር ነውና የሚያምረው ጮክ ብለህ ለመሳቅ እንኳን ከልብሀ አዉጥተሀ ለማልቀስ እንኳን በሃገር ነዉና ሀገራችን በሠላም በአንድነት እንድትኖር ሁላችን እጅ ለእጅ በመያያዝ ለሀገራችን ክብርና ሠላም በአንድነት እንቁም🇪🇹 ሠላም አንድነት እድገት ብልፅግና ከመላው ሕዝቧ ጋር ለዘላለም ይሁን 🇪🇹 ኢትዬጵያ ለዘላለም ትኑር 🇪🇹

K the Valencia

Scroll al inicio