በእስፔን ስኬታማ ስብስባ ተካሄደ

በስፔን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የስፔን ዜጎች፣ ለሀገራቸው ያላቸውን ክብር በድጋሚ አረጋግጠዋል

በስፔን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የስፔን ዜጎች፣ ለሀገራቸው ያላቸውን ክብር በድጋሚ አረጋግጠዋል፣ በ05/06/2022 በተደረገዉ የዙም ስብሰባ ዛሬም በድጋሚ ሀገራቸውን ኢትዮጵያን ለመርዳት ቁርጥ አቁዋማቸዉን   አሳይትዋል ይህ ስብሰባ በኮሙኒዳድ ዴ ኤትዮጴስ ኤን ኤስፓኛ አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን በፓሪስ የኢትዮጵያ ተወካይ ተጋብዘዉ ተገኝተዋል።

የኤምባሲዉ ተወካይ አቶ ሰለሞን  ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጥልቅ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስፔናውያን በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በተከሰቱት ጦርነቶች የፈረሰችውን አገራችንን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ዉስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ አብራርተው ጋብዘዋል።

በዙም ስብሰባ ላይ የተገኙትም በበኩላቸው በአገራቸው ባለው አቅም ለመተባበር ፈቃደኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ስለ ሰላም መስፈን፣ በመንግስት የተወሰዱ እርምጃዎች፣ በሰሜን በተካሄደው ጦርነት ምክንያት የተለያዩ ተቋማትን መልሶ ስለመገንባት፣ እንደ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ በርካታ ጥያቄዎችና መልሶች ተነስተዋል።

በተጨማሪም ከተሰብሳቢዎቹ ከቪዛ ጉዳይ ጀምሮ ሌሎች  ግልጋሎቶችን  ለማግኘት በአንዳንድ ቦታ ያለዉን አስቸጋሪ ሁኔታ በማንሳት ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ተወካዩ ጉዳዩን ከሚመለከታቸዉ ተቁዋማት ጋር በመነጋገር እርምት እንዲወሰድ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በፓሪስ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተወካይ አቶ ሰለሞን በአውሮፓ ለሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ሰለሃገራችዉ የጠለቀ ግ ንዛቤ መረጃ በመስጠት  በስፋት እየተንቅሳቀሱ ያሉ ብርቱ የኢትዮጵያ ተወካይ ሲሆኑ በቅርቡም  በ 29/05/2022 በፈረንሳይ፣ በፖርቱጋል እንዲሁም በእስፔን ለሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የጠለቀ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Exsito en el encuentro de Zoom realizado por la comunidad de Etíopes en España y el representante de la Embajada de etíopes en Paris.

Los residentes etíopes  en España y los españoles de ascendencia etíopes hoy 05/06/2022 tuvieron una reunión con el representante de la embajada etíope en Francia y se habló importantes tópicos y fue un éxito.

El representante de la embajada, Ato Solomon Zekie, brindó un relato detallado de la situación actual en Etiopía e invitó a los etíopes y etíopes de ascendencia etíope a participar en los esfuerzos para reconstruir nuestro país devastado por la guerra en el norte del país.
Por su parte, los presentes en el encuentro de zoom  reafirmaron su voluntad de trabajar juntos por los intereses de su país y su pueblo.
En la reunión surgieron muchas preguntas y respuestas sobre la paz, la acción del gobierno para restablecerlo, la reconstrucción de varias instituciones dañadas debido a la guerra en el norte, como tales hospitales, escuelas y universidades.

Los presentes en el encuentro también plantearon el problema que hay para adquirir servicios, citando ejemplo el problema en el  visado y el representante aseguro que el informara y trabajará con las autoridades pertinentes para rectificar la situación.

El representante de la Embajada de Etopa en París, Ato Solomon, esta hacienodo un gran labor para que los etiopes que viven en europa tenga una información utili y verdader acreca de su pais natal .

Este encuentro fue organizado por la Comunidad de Etiopes en España.

Scroll al inicio