ኢትዮጵያ ያከበሩዋትን ታላቅ ሰዎች ታከብራለች
ሌሎች በችግራችን ግዜ ፍቅር ሲሰጡን እኛም በችግራቸው ግዜ ፍቅር መስጠት እንደምናውቅ በተግባር እናሳይ ታሪኩን ይመልከቱ
Etiopía honra a grandes personas.
Cuando otros nos dan amor en nuestro momentos de necesidad y dificultad, nostros tambien debemos hacerlo en sus momentos complicados, pongámoslo en práctica. Mirar la historia completa en el video.
ይህ ነዉ የሚያምርብን
ነፃነት ፣ታሪክ፣ ፍቅር ፣ ልዩ ልዩ ጥዑም ባህል ፣ ሰንድቅ የአባቶቻችን ዉድ የዉርስ ጌጥ እያንዳንዱ ሲጠርዝ ኢትዮጵያን ይሰጣል ፣ ይህ ነዉ ዉርሳችን። እንግዲያዉስ መበጥረቅን፣ መብሰክሰክን ፣ መዋተትን ፣ተንኮል መቆፈረን አሽቀንጥረን ጥለን ይህን የአባቶቻችን ትልቅ ስጦታ ጥሮ ግሮ ሰርቶ ወደ ሚቀጥለዉ ደረጃ መዉሰድ የአሁኑ ትዉልድ ግዴታና ሃላፊነት ይሆናል።
ለትዉልድ የተበረከተ የአባቶቻችን የታሪክ አሻራ
ይህ ህያዉ የሆነ የነፃነት ምስል ዳቦ ለመለቃቀም በሰዉ ሃገር ወጥተዉ እንድሸለምጥማጥ የራስ ባልሆነ ግን ብልህ ሰዎች በሰሩት የሰልጣኔ ግርግዳ ላይ እየተሳቡ Ethiopia down down ለሚሉ የመንፈስ ደዌዎች ህክምና ይሆናቸዉ ዘንድ የቀረበ የታሪክ ህክምና ነዉ። ይህም ታሪክ ቂጣ ቆሎ እየቆረጠሙ በባዶ እግራቸዉ ወጥተዉ ወርደዉ ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቀዉ የነፃነት የአንድነት ምልክቱን ዉድ የዉርስ ጌጡን አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቁን በልባችን በጥልቀት ሸንቁረዉ በመትከል በታሪክ በባህል በተፈጥሮ ሃብት የታደለች ትልቅ ሃገር ያቆዩዋት የቆፍጣናዎቹ አባቶቻችን አሻራ ክታብ ነዉ። ይህ ኩራት ተብሎ ይጠራል ። ነገር ግን ይህንን ትልቅ ታሪክና ሃገር ማስጠበቅ እና ከድህነት ለመውጣት መስራት የአሁን ትውልድ ሃላፊነትና ግዴታ ነዉ።
La gran contribución de nuestros antepasados
Esta imagen viva de la libertad es una cura histórica para la lepra que se arrastra por los muros de un mundo civilizado diciendo “abajo Etiopía, abajo Etiopía” esta es la huella de nuestros antepasados, que lucharon con recursos agotados y sin embargo mantuvieron a nuestra generación una gran nación con historia, rica en diversidad cultural y recursos naturales. Esto se llama historia, ahora bien, mantenerlo y trabajar para salir de la pobreza le corresponde a la generación actual.
